አዲስ አበባ የካቲት 1/2002(ሬዲዮ ፋና) የህብረቱ ጽህፈት ቤት አዲስ አበባ ውስጥ ከመሆኑ ጋር በተያያዘ ዛሬ የአባል አገሮቹ አምባሳደሮችና የተለያዩ ዓለማቀፍ ተቋማትና ሀገሮች ተወካዮች ለህብረቱ መደረግ ባለበት ድጋፍ ዙሪያ ተወያይተዋል።
በዚሁ ወቅት የህዝብ ተወካዮች ምክር ቤት አፈጉባኤና የህብረቱ ምክትል ፕሬዝዳንት የተከበሩ አምባሳደር ተሾመ ቶጋ እንዳሉት ህብረቱ የያዛቸውን ዓላማዎች ከግብ ለማድረስ ዘርፈ ብዙ ድጋፎች ያስፈልጉታል።
በቀጠናው ያለውን የሰላምና የጸጥታ ችግር መፍታት፣መንግስታት ለሚሰሯቸው የልማት ስራዎች ስኬት እገዛ ማድረግና የህዝብ ለህዝብ ግንኙነትን ማጠናከር ከህብረቱ ዓላማዎች ውስጥ ዋነኞቹ መሆናቸውንም አምባሳደር ተሾመ አብራርተዋል።
የውይይቱ ተካፋዮችም በሰጡት አስተያየት ስለህብረቱ በቂ ግንዛቤ መጨበጣቸውን፣የያዛቸው ዓላማዎችም ተገቢ መሆናቸውንና አስፈላጊውን ድጋፍ እንደሚያደርጉ አረጋግጠዋል።