Skip Navigation Links    
     





 

 
የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ከሰጠው ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር 98 በመቶው ተመላሽ ሆነ

Saturday, July 31, 2010

 
     
   

አዲስአበባሐምሌ24 2002 (ሬዲዮፋና) የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም ባለፈው አመት ከሰጠው  ሁለት ቢሊዮን ብር የሚጠጋ ብድር  98 በመቶውን በወቅቱ ተመላሽ ሆኗል አለ። በአሁኑ ስዓት 720 ሚሊዮንብር  ካፒታል ያለው ሲሆን፣ ለተጠቃሚዎቹም ከ5 ሚሊዮን ብር በላይማበደር ችሏል የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም።

 

 

               ተቋሙብድር ከመስጠት በተጨማሪ ደንበኞቹ የቁጠባ ባህላቸው እንዲዳብር ከፍተኛ እንቅስቃሴ እያደረገ መሆኑንም ገልጿል  ።

 

               የዛሬ7 አመት  በ3ሚሊዮን ብር ካፒታል ነበር የተቋቋመው ።

 

       በአሁኑ ስዓት720 ሚሊዮን ብር  ካፒታል ያለው ሲሆን፣ ለተጠቃሚዎቹም እስከ 5ሚሊዮን ብር በላይ ማበደር ችሏል የአማራ ብድርና ቁጠባ ተቋም።

 

       የተቋሙ  ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ መኮነን የለውምወሰን ለሬዲዮ ፋና እንዳሉት ተቋሙየደንበኞቹን የገንዘብ እጥረት ለማቃለልና ወደ ፈለጉት የስራ መስክ እንዲሰማሩ የገንዘብ አቅሙን ከጊዜ ወደ ጊዜ እያሳደገ ነው።

 

        ባለፈውዓመት ቢቻ ከ1ቢሊዮን 900 ሚሊዮን ብር በላይ ለተጠቃሚዎች አበድሯል ነው ያሉት።

 

       ተቋሙ በእስካአሁንሂደቱ በብድር አመላለስ ላይ ምንም ችግር ያልነበረበት ነው ያሉት አቶ መኮነን ከሚወሰድው ብር በአማከኝ 99በመቶ በወቅቱተመላሽ ይሆናል ብለዋል።

 

          ይሁን እንጂባለፈው ዓመት ቢቻ ከተውሰደው ብድር 30 ሚሊዮን የሚሆን ብር በወቅቱ መመለስ ያለበት ግን ያልተመሰ እንዳለ ይናገራሉ።

 

        በተለይምበአቆራጭ መበልፀግ  የሚፈልጉና ብድር ወስደው የሚሰወሩ እንዳሉጠቁመዋል።ይሁን እንጂ ገንዘቡን በአጭር ጊዜ ለመመለስና ችግሩን ለማስወገድ ከፍተኛ ጥረት እየተደረገ ይገኛል።

 

ተቋሙ ብድር ከመስጠት በተጨማሪም ደንበኞቹ የቁጠባ ባህላቸው እንዲዳብርም እየሰራ ይገኛል።

 

ተቋሙ በአሁኑ ጊዜ 50 በመቶ የሚሆነው የብድር አቅርቦቱ በቁጠባ በሚሰበሰብ ብድርእንደሚሸፈን ነው የተናገሩት አቶ መኮንን ። ባለፈው ዓመትም ከፍተኛ መጠን ያለው ገንዘብ መቆጠቡን ይናገራሉ።

እንደ አቶ መኮነን አነጋገር ከሆነ መቶ በመቶ የብድር አቅርቦቱን በቁጠባ ለመሸፈን እቅድይዞ እየተንቀሳቀሰ ነው።

 

እንዲሁም የተቋሙ ተቀማጭ ገንዘብ በአሁኑ ስዓት 720 ሚሊዮን ብር በመሆኑ በሚቀጥለውአመት ለአንድ ደንበኛ እስከ 10 ሚሊዮን ብር ለማበደር የሚያስችለውን  እቅድ ይዟል።  

 

 
     
 
Other Stories

ወደ አገር ውስጥ የሚገባው ቀጥተኛ የውጭ ኢንቨስትመንት ፍሰት እያደገ ነው

በመረጃ ነጻነት ህግ ዙሪያ የተዘጋጀው የምክክር መድረክ ተጠናቀቀ

የተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት የተረጋጋ የኢኮኖሚ መሠረት መጣሉን የዓለም ገንዘብ ድርጅት አመለከተ

በአበባ እርሻ ልማት ዘርፍ የተሰማሩ ድርጅቶች 250 ሚሊዮን የአሜሪካ ዶላር ገቢ አገኙ

ከጨርቃ ጨርቅ ኢንዱስትሪው ዘርፍ አገሪቱን ተጠቃሚ የሚያደርጉ ተግባራት እየተከናወኑ ነው

በተመዘገበው የኢኮኖሚ ዕድገት የኅብረተሰቡ አኗኗር መቀየሩን በኢትዮጵያ የጃፓን አምባሳደር ገለፁ

የምንዛሬ ተመን ማስተካከያው የተጀመረውን ዕድገት ለማስቀጠል ይረዳል ተባለ

የመረጃ ነጻነት ህግ አገራዊ ተፈጻሚነት እንዲኖረው ነጻ በሆነ መልኩ መፈጸም ይኖርበታል ተባለ

የውጭ ምንዛሪ ተመን ለውጡ የወጪ ንግድን ለማጠናከር ይረዳል --- የኢትዮጵያ ንግድና ዘርፍ ማህበራት ምክር ቤት

አዲሱ የከፍተኛ ትምህርት መመሪያ ጥራትን ለማረጋገጥ የተቀረፀ መሆኑ ተጠቆመ