አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23 2002 (ሬዲዮ ፋና) ሀገራችን ከአበባ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ መጠን በቀጣዮቹ አምስት አመታት ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ለማድረስ እንቅስቃሴ እየተደረገ መሆኑ ተጠቆመ።
የኢትዮጵያ የአበባ አትክልትና ፍራፍሬ አምራችና ላኪዎች ማህበር ሊቀ መንበር አቶ ጸጋዬ አበበ ለሬዲዮ ፋና እንደተናገሩት ኢትዮጵያ በአሁኑ ወቅት ከዘርፉ የምታገኘው አመታዊ ገቢ 216 ሚሊን ዶላር ብቻ ነው።
ይህንን ገቢ በየአመቱ በ30 በመቶ በማሳደግ ሀገራችን ከአምስት አመታት በኋላ ከአበባ ፣ አትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ የምታገኘውን የውጭ ምንዛሪ ወደ አንድ ቢሊየን ዶላር ለማድረስ የታቀደው።
ጎረቤት ኬኒያ፤ ግብጽና ሞሮኮ በየአመቱ ከአትክልትና ፍራፍሬ ዘርፍ ብቻ ከግማሽ ሚሊየን ዶላር በላይ ገቢ እንደሚያገኙ ገልጸዋል።
ልማቱ ተግባራዊ ሲደረግም ከዘርፉ ወደ 1 ቢሊየን የሚጠጋ ገቢ እንደሚገኝና ለ200 ሺ ሰወች የስራ እድል እንደሚፈጠር ሊቀ መንበሩ ጠቁመዋል።
ይህም የዘርፉን ገቢ ለማሳደግ ጠንካራ ስራ መስራት ይገባል ማለታቸውን ባልደረባችን አምሳለ ተስፋዬ ዘግባለች።