አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 23 2002 (ሬዲዮ ፋና) በምርት ጥራታቸውና በውጨ ገበያ ተፈላጊነት ያላቸው 51 አዳዲስ የሰብል ዝርያዎችን በምርምር አሻሽሎ መልቀቁን የኢትዮጵያ ግብርና ምርምር ኢንስቲትዩት አመለከተ።
የሰብል ምርምር ውጤቶች ለስምንት ዓመታት ምርምር ሲካሄድባቸው ከቆየ በኋላ ውጤታማነታቸው ተረጋግጦ ባለፈው በጀት ዓመት ተሰራጭተዋል።
ከተለቀቁት ዝርያዎች መካከል ሰሊጥ፤ ለውዝ፤ አኩሪ አተር፤ ሩዝ፤ ድቃይ በቆሎ፤ ስንዴና ሌሎች አትክልትና ፍራፍሬዎች ይገኙበታል።