አዲስ አበባ፣ሐምሌ 23 2002 (ሬዲዮ ፋና) ኢትዮጵያ ስደተኞችን በመቀበልና በመንከባከብ ከዓለም ጥቂት ሃገራት ተርታ እንደምትሰለፍ ተጠቆመ።
የብሄራዊ መረጃና ደህንነት አገልግሎት የስደተኞችና ከስደት ተመላሾች ጉዳይ አስተዳደር እንዳለው ኢትዮጲያ ከተለያዩ ሃገራት የሚመጡ ስደተኞችን በመቀበል፤ የመጠለያ ጣቢያዎችን አዘጋጅቶ ሰብዓዊ መብታቸውን በመጠበቅና በመንከባከብ ረገድ በዓለማችን በቀዳሚነት ከሚጠቀሱ ሀገሮች ተርታ ትሰለፋለች።
ዓለም አቀፍ የስደተኞች አያያዝ ኮንቬንሽንን የዛሬ 51 አመት እንደፈረመችና በሕገ መንግስቷም የስደተኞችን አያያዝ የሚመለከት አንቀፅ ደንግጋ ተግባራዊ እያደረገች እንደምትገኝ ዋልታ ዘግቧል።
በኢትዮጵያ 110 ሺ የኤርትራ የሶማሊያና የደቡብ ሱዳን ስደተኞች ይገኛሉ።