አዲስ አበባ፣ ሐምሌ 22 2002 (ሬዲዮ ፋና) የደረቅ ወደብ አገልግሎት ደርጅት በሞጆ ደረቅ ወደብ የሰባት ሄክታር ኮንቴይነር ማስተናገጃ ተርሚናል ለማስገንባት የሚያስችል ስምምነት ተፈራረመ።
ድርጅቱ ስምምነቱን የተፈራረመው ግንባታውን ከሚያካሄደው ከውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ጋር ነው።
ስምምነቱን የተፈራረሙት በደረቅ ወደብ አገልግሎት ድርጅት በኩል ዋና ስራ አስኪያጁ አቶ እውነቱ ታዬ እና የውሃ ስራዎች ኮንስትራክሽን ድርጅት ዋና ስራ አስኪያጅ አቶ አበበ አየነው ናቸው፡፡
ግንባታው የሚካሄደው ከ254 ሚሊዮን ብር በላይ በሆነ ወጪ እንደሆነ የባልደረባችን ታደሰ ብዙአለም ዘገባ ያመለክታል ፡፡
ግንባታው ሲጠናቀቅም የሞጆ ደረቅ ወደብ በዓመት የሚያስተናግደውን 28 ሺ 280 ኮንቴይነር ወደ 110 ሺ 373 ከፍ ያደርገዋል፡፡